
ቶፐር ኑረቲን ካራኩንዳኮ በተባሉ ምጡቅ የቴክኒክ ባለሞያ እ፣ኤ፣አ በ1954 በ33 ካሬ ሜትር ይዞታ ላይ የተቋቋመ ነው፡፡ ሚ/ር ኑርቲን ጠንክሮ በመስራቱ በወቅቱ የብዙ ቡና ቆይዎችን ትኩረት ለማግኘት ችሏል፡፡ሚ/ር ኑርቲን ከባለቤቱ ሚስዝ ዘኪዬ ጋር በመደጋገፍ በዓመት 300 የስንዴ ወፍጮና የተለያዩ ማሽነሪዎችን ያመርት ነበር፡፡
.እ፣ኤ.አ በ 1970 የነበረው ሁለተኛው የቤተሰቡ ትውልድ ሁሉም የቴክኒክ ዕውቀት የነበራቸው ሲሆን እ፣ኤ.አ በ 1980 ምርቶቻቸው በምርምር የተደገፉ ስለነበሩ እንደ ሊቢያና ዩጎዝላቪያ የመሳሰሉ ሀገራት በምርቶቹ መሳብ ጀመሩ፡፡
የቀዳሚ ባለሞያዎቹ የእነ ኑረቲን የዳበረ ልምድ በአዲሱ ትውልድ ምርምር እየተደገፈ የቶፐር ምርቶች በሮማንያ ካናዳና አሜሪካም መላክ ጀመሩ፡፡ከዚያም የቡና መቁያ መሳሪዎያዎች የቡና ቁሌት የሚወስደውን ጊዜ ወደ 9 ደቂቃ በማውረድ ከታዋቂው የቱርክ የምርመርና የቴክኒክ ካውንስል ጋር በትብብር በመስረቱ የብዙ ብቃት ማረጋጋጫ ባለቤት ለመሆን ቻለ ፡፡ የቤተሰቡ 3ተኛ ትወልድም በተለያዩ የሙያ መስኮች የሰለጠነና የካበተ ልምድ ስላገኘ ቶፐር በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ ካሉ 8 ምርጥ የቡና ማቀነባበሪያ ብራንድ ውስጥ መካተት ችሏል፡
ይህ በሚ/ር ኑረቲን በ1954 ዓ.ም የተለኮስው ብርሃን ዛሬ በ146 የዓለም ሀገራት በማንጸባረቅ ላይ ይገኛል፡፡

