የቡና ማሸጊያ

የተመረተ ቡና ለማሸግ የተዘጋጁ ማሽኖች ሲሆን ቡና ከተፈጨ በኋላ በሚታሸግበት ጊዜ በውስጡ ያለው አየር አብሮት ወደ ማሸጊያው ሲገባ ቡናውን ለረጅም ጊዜ እንዳይቆይ ስለሚያደርገው ይህ ማሽን ቡናው በሚታሸግበት ወቅት አየሩን አስወጥቶ የሚያሽግ ነው፡፡

አንዳንድ ጊዜ የቡናውን ዕድሜ ለማራዘም ተብሎ በቴክኖሎጂ የተመረቱ ጎጂ ያልሆኑ ጋዞችን በማሸጊያው ውስጥ ከመርጨት ይልቅ ይህ ማሽን የተሻለ አማራጭ ነው፡፡ ይህ ማሽን ባለ 250 ግራምና ባለ 500 ግራም የሚታሸግ ቡናን በአንድ ጊዜ ሊያሽግም ይችላል፡፡